amharic

በኦርቶዶክስ ገዳም ውስጥ ከተደረገ የተኩስ ልውውጥ በኋላ ኮሶቮና ሰርቢያ ተፋጠጡ

የሰርቢያ የዘር ሀረግ ያላቸው ታጣቂዎች እና የሰሜናዊ ኮሶቮ ፖሊስ ግጭት ውስጥ ከገቡ በኋላ ኮሶቮ እና ሰርቢያ እርስ በርሳቸው እየተካሰሱ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያዊቷ ትዕግስት አሰፋ የዓለም የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን ከሁለት ደቂቃ በላይ አሻሻለች

ዛሬ እሑድ መስከረም 13/2016 ዓ.ም በጀርመን በርሊን በተካሄደ 48ኛው የሴቶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግሥት አሠፋ የዓለም ክብረወሰንን በመስበር አሸነፈች። ትዕግሥት 2:11:53 በመግባት ነው ውድድሩን በማሸነፍ ክብረ ወሰን መስበር የቻለችው።

በአዲስ አበባ ከተማ ሕጋዊ ሥርዓትን ያልተከተሉ የጅምላ እስሮች ቀጥለዋል – ኢሰመጉ

በአዲስ አበባ ከተማ ሕጋዊ ሥርዓትን ያልተከተሉ እና አንዳንዶቹም አስገድዶ የመሰወር ባህርይ ያላቸው የጅምላ እስሮች መፈፀም መቀጠላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አስታወቀ። ኢሰመጉ በመግለጫው የሚመለከታቸው አካላት እነዚህን ከሕግ አግባብ ውጭ የተፈፀሙ እስሮች ለማስቆም እርምጃ ባለመውሰዳቸው አሁንም የጅምላ እስሮች ቀጥለዋል ብሏል።

በቤኒን ሁለት ሕጻናትን ጨምሮ 34 ሰዎች በእሳት አደጋ ሞቱ

ቤኒን ከሰሜናዊ ናይጄርያ በምትዋሰንበት የድንበር ከተማ አቅራብያ ቅዳሜ ዕለት በተነሳ እሳት ከ30 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ።በእሳት አደጋው ተቃጥለው ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ፣ 20 ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ በመጎዳታቸው ሆስፒታል ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ነው ተብሏል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት(ኤአይ) የተሰሩ የሕጻናት እርቃን ምስሎች በስፔን ድንጋጤ ፈጠሩ

በደቡባዊ ስፔን የምትገኘው አልመንድራሌሆ ከተማ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች እርቃን ምስሎች ከእነርሱ እውቅና ውጭ በማኅበራዊ ሚዲያ ከተዘዋወሩ በኋላ ድንጋጤ ውስጥ ገብታለች።

Popular

spot_imgspot_img